دسترسی به ترابایت پورن در تلگرام »

Ethiopian Jobs - የስራ ማስታወቂያ

لوگوی کانال تلگرام ethiopian_jobs1 — Ethiopian Jobs - የስራ ማስታወቂያ E
آدرس کانال: @ethiopian_jobs1
دسته بندی ها: محتوای بزرگسالان (18+)
زبان: فارسی
مشترکین: 38
توضیحات از کانال

የኢትዮያዊያንን የትምህርት የስራ አንዲሁም የማህበራዊ ህይወት የተሻለ ለማድረግ የሚረዱ መረጃዎችን ማቅረብ ነው። ስራችን እንደ ስማችን ኢትዮጵያዊ ለዛ ያለው ነው።
#ለማስታወቂያ እና ለጥቆማ 👉 @antenehg1
በውስጥ መስመር ያነጋግሩን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


آخرین پیام ها 17

2021-01-12 22:18:06 ለቸኮለ! ማክሰኞ ጥር 4/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የሱዳን ጦር ሃይል በጋራ ድንበሩ አካባቢ የጀመረውን ሕገወጥ እንቅስቃሴ እያሰፋ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ዜና አውታሮች ዘገብዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ግጭት ይጠቅማል ብላ እንደማታምን ተናግረዋል፡፡ አካባቢ እየተስፋፋ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡ የሱዳን ድርጊት ዐለማቀፍ ሕግን የተጻረረ እንደሆነም ዲና ተናግረዋል፡፡

2፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሦስት ወረዳዎች ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ጀርመን ድምጽ ዘግቧል፡፡ ከሐሙስ ጀምሮ እስከ ትናንት ታጣቂዎች ጥቃቶችን የፈጸሙት፣ በመተከል ዞን ጉባ፣ ወንበራ፣ ድባጤ እና ቡለን ወረዳዎች ነው፡፡ በጉባ ወረዳ ብቻ ትናንት 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ባለፈው ሐሙስ ደሞ በወንበራ ወረዳ 16 ሰዎች ተገድለዋል- ብሏል ዘገባው፡፡

3፤ ዐቃቤ ሕግ የእነ ጃዋር ሞሐመድን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ማዘዙን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መከላከያ አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎ፣ ለጥር 14 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የተከሳሾቹ የክስ መከላከያ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለው በመጥቀስ፣ ጉዳዩ ወንጀሉ ተፈጸመ በተባለበት በኦሮሚያ ክልል እንዲታይ የሚጠይቅ ነው፡፡ የክስ መከላከያውን ያቀረቡት ጀዋር እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ተከሰሾች ናቸው፡፡

4፤ ለፓርላማ የቀረበው የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ በርካታ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው ባለ 33 ገጽ ሪፖርት፣ ረቂቅ ሕጉ ከሰብዓዊ መብቶች አንጻር የሚቀሩት ማሻሻያዎች አሉ፡፡ ኮሚሽኑ ማሻሻያ ሃሳቦቹን ያቀረበው በ30 ድንጋጌዎች ላይ ሲሆን፣ የማሻሻያ ሃሳቡንም ለፓርላማው እና ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅርቧል፡፡

5፤ በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በቅርስነት የተመዘገበውን የደጅ አዝማጅ አስፋው ከበደ መኖሪያ ቤትን እንዳፈረሰው ሸገር ዘግቧል፡፡ ቤቱን ከመፍረስ ለመታደግ የቅርስ እና ጥበቃ ባለሥልጣን ሃላፊዎች ሙከራ አድርገው ነበር፤ ሆኖም በማፍረሱ ሂደት ወቅት ወታደሮች ወደ ግቢው እንዳይገቡ እንደከለከሏቸው ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡ በቅርስነት የተመዘገበው መኖሪያ ቤት እቴጌ መነን ትምህርት ቤት ፊተ ለፊት የሚገኝ ነው፡፡

6፤ የአንበጣ መንጋ በሰሜን ኬንያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እየተስፋፋ እንደሆነ የተመድ እርሻ ድርጅት ባወጣው ዜና አስታውቋል፡፡ ገና ዕድገቱን ያልጨረሰው የአንበጣ መንጋ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ሱማሊያ የተነሳ ነው ተብሏል፡፡ አንበጣ መንጋው የኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ የሰሜን ኬንያ ግዛቶች ካሁኑ በስፋት መታየት ጀምሯል፡፡ በአካባቢው ያለው ደረቅ አየር አንበጣው በፍጥነት እንዲስፋፋ እንደሚግዛው ተነግሯል፡፡

7፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች በድንበር አካባቢ በፈጸሙት ጥቃት አንድ ሕጻንን ጨምሮ 6 ሰላማዊ ዜጎች ሞተዋል ሲል ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ጥቃቱ ሰኞ’ለት ተፈጸመ የተባለው በገዳሪፍ ግዛት አል-ቁራይሻ በተባለ አካባቢ ነው፡፡ ስለ ዘገባው ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ካሁን ቀደም ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ የተዛባ ዘገባ አሰራጭቷል በማለት መውቀሱ ይታወሳል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
11.4K views19:18
باز کردن / نظر دهید
2021-01-10 22:16:13 ከገበያ ቻናላችን እቃ የሚገዛ 1 ጓደኛዎን/ወዳጆን ሲያመጡ ለርሶ የ50ብር-ካርድ ይበረከትሎታል! እድሉን ይጠቀሙ፣ ይሸለሙ!

በአዲስአበባ እና በሁሉም የሀገራችን ከተሞች የተለያዩ ዘመን አመጣሽ እቃዎችን እያደረስን እንገኛለን። ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ።

Online ይገበያዩ፣ ይግዙ፣ ይሸለሙ!
"ጥራት እና ታማኝነት መለያችን ነው።"
++The Most Trusted Channel In Ethiopia++
9.0K views19:16
باز کردن / نظر دهید
2021-01-06 23:31:58 ለቸኮለ! ረቡዕ ታኅሳስ 28/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የብሄራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር. ተመስገን ጥሩነህ ተቋሙን እንደገና ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ ተመስገን የተቋሙ ሃላፊ ከሆኑ ወዲህ፣ ከከፍተኛ እስከ ታች ያሉ ከ200 በላይ የሥራ ሃላፊዎችን ከእነ ደመወዛቸው ግዳጅ እረፍት አስወጥተዋል፡፡ ዋዜማ በሀገሪቱ ጸጥታ ችግሮች እጃቸው እንዳለበት እና ለታጣቂ ሃይሎች ሚስጢር በማቀበል ተጠርጥረው ግዳጅ ፍቃድ የወጡ 27 ሠራተኞችን ስም ዝርዝርም አግኝታለች፡፡

2፤ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾችን ረጅም የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደገና ለመወሰን ፍርድ ቤት ለጥር 5 እንደቀጠረ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ ለምስክሮች መስሚያ ጊዜ ቀደም ሲል ለመጋቢት መጨረሻ የሰጠውን ቀጠሮ እንደገና ለማየት ተከሳሾቹ ለመጭው ሐሙስ በአካል እንዲቀርቡ ችሎቱ ለጠበቆቻቸው አሳውቋል፡፡

3፤ ፍርድ ቤት የአማጺው ሕወሃት ከፍተኛ አመራር በሆኑት አዲስ ዐለም ባሌማ ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደፈቀደ ሸገር ዘግቧል፡፡ አዲስ ዐለም ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች አንዱ አውሮፓ ኅብረት በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጥር ቀስቅሰዋል፤ በትግራይ ክልል በመንግሥት ተቋማት ጠባቂ ፌደራል ፖሊሶች ላይ የሕወሃት ሃይሎች ለፈጸሙት ጥቃት ተባባሪ ነበሩ የሚል ነው፡፡

4፤ ሱዳን የጋራ ድንበር ውዝግብ አፈታት ስምምነትን ጥሳለች ሲል የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ኮሚሽን መክሰሱን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ዛሬ ለመንግሥት ዜና አውታሮች በሰጡት ቃል ውንጀላውን ያሰሙት የኮሚሽኑ አባል አምባሳደር ኢብራሂም እድሪስ ናቸው፡፡ ሰሜን ዳግሊሽ የጠባለው አካባቢ ድንበሩ በሁለትዮሽ እና በዐለማቀፍ ሕግ መሠረት እስኪካለል ድረስ ባለበት ነባራዊ ሁኔታ እንዲቆይ እኤአ 1972 ሁለቱ መንግሥታት የተስማሙ ቢሆንም፣ በቅርቡ ግን የሱዳን ጦር አካባቢውን በሃይል ጥሶ ገብቷል፡፡

5፤ ሕዝቡ የተለያዩ ጽሁፎች ወይም ምልክቶች ያረፉበትን የወረቀት ገንዘብ መቀበል እንደሌለበት በማኅበራዊ ሜዲያ የሚሰራጨው መረጃ መሠረተ ቢስ ወሬ መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በወረቀት ገንዘብ ላይ መጻፍ፣ መቅደድ፣ ማበላሸት ወይም ባግባቡ አለመያዝ ግን ድሮም በሕግ የሚያስጠይቅ ድርጊት መሆኑን ባንኩ አስታውሷል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው አዲስ ወረቀት ብሮች ከገበያው ስለሚወጡበት ሁኔታ ባንኩ መመሪያ እያረቀቀ እንደሆነም አክሎ ገልጧል፡፡

6፤ የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ወገን የተቃጡ 2 ጥቃቶችን ማክሸፉን ከጦሩ ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ ሰኞ’ለት ከኢትዮጵያ ወገን ጥቃት ተሰነዘረ የተባለው፣ ፋሻጋ በተባለው የትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታ ነው፡፡ በግጭቱ የሱዳን ጦር ሃይል አንድ የኢትዮጵያ ወታደር ማርኬያለሁ ማለቱን ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡ የሱዳን ጦር ሃይልም ይሁን የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ለዚሁ ዘገባ ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡ በተያያዘ ዜና፣ ድንበር ላይ ስላሉ እንቅስቃሴዎች ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨ ነው በማለት በካርቱም የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዛሬ ከሷል፡፡

7፤ አሜሪካ የሱዳንን የዐለም ባንክ ዕዳ ለመክፈል የሚያስችላትን ስምምነት የአሜሪካው ግምጃ ቤት ሚንስትር ስቲቨን ሙነችን ዛሬ በካርቱም ተገኝተው እንደፈረሙ የሱዳን ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡ ሱዳን የተከማቸ ዕዳዋ ከተሰረዘላት፣ ወደፊት ከባንኩ ዐመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ የሱዳኑ ወታደራዊ ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል-ቡሕራን ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ስለገባችበት የድንበር ፍጥጫ ለሙነችን አብራርተውላቸዋል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
11.3K views20:31
باز کردن / نظر دهید
2021-01-05 18:52:50 ለቸኮለ! ማክሰኞ ታኅሳስ 27/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የቀድሞው መንግሥት ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌ/ጄኔራል አዲስ ተድላ ከጣሊያን ኢምባሲ ወጥተው ቤታቸው እንደገቡ የጀርመን ድምጽ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሁለቱ ግለሰቦች በኢምባሲው ለ30 ዐመት በጥገኝነት ቆይተዋል፡፡ ግለሰቦቹ በነጻነት ከኢምባሲው የወጡት፣ ከተወሰነባቸው ዕድሜ ይፍታህ ፍርድ በአመክሮ ነጻ እንዲሆኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በወሰነው መሠረት ነው፡፡

2፤ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ በንግግር ብቻ እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግሥት ፍላጎት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ሚንስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ ያሁኑ የድንበር የተፈጠረው ችግር ከሁለቱ ሀገሮች ታሪካዊ ወንድማማችነት ጋር የሚጣረስ መሆኑንም ዲና ተናግረዋል፡፡ ከኅዳር መባቻ ጀምሮ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ በከባድ ወታደራዊ ካሚዮኖች የታገዘ ጥቃት ሲፈጽም መቆየቱንም ዲና በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

3፤ የሕዳሴው ግድብ ድርድር ዛሬ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡ ትናንት በስብሰባው ያልተገኘችው ሱዳን ዛሬ ትገኝ አትገኝ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት አልታወቀም፡፡ ወደፊት በአባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ግን ሀገራቱ ሰፊ ልዩነት እንዳላቸው የውሃ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡ ድርድሩ ሳይስተጓጎል ከቀጠለ፣ በመጭው ዕሁድ ለሚንስትሮች ሪፖርት ይቀርባል፡፡

4፤ በትግራዩ ግጭት ጉዳት የደረሰበትን አል ነጃሺ መስጊድ መንግሥት እጠግናለሁ ማለቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡ ውቅሮ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አል ነጃሺ መስጊድ እና ባንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም አንድ ቡድን እንደሚላክ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ሃላፊ አበባው አያሌው ተናግረዋል፡፡ በመስጊዱ እና በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ለደረሰው ጉዳት እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም፡፡

5፤ ከኢትዮጵያው ኦጋዴን ወደ ጅቡቲ የጋዝ ቧንቧ ለመዘርጋት መንግሥት ዐለማቀፍ ጨረታ እንደሚያወጣ ሪፖርተር የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስትሩን ታከለ ኡማን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧውን የሚገነባው የውጭ ኩባንያ ሲሆን፣ ንብረትነቱ እና አስተዳደሩ ግን በመንግሥት ስር እንደሚሆን ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡ በኦጋዴኖቹ ካሉብ እና ሒላል አካባቢዎች የእንግሊዝ እና ቻይና ኩባንያዎች የተፈጥሮ ጋዝ በማልማት ላይ ናቸው፡፡

6፤ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር በዋሉ 5 ጄኔራል መኮንኖች እና 10 ኮሎኔሎች ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምርመራ ላይ ካሉት መካከል፣ የመከላከያ ሠራዊትን ራዲዮ መገናኛ በማቋረጥ የተከሰሱት ሜ/ጄኔራል ገ/መድኅን ፍቃዱ ይገኙበታል፡፡ በወንጀል የሚፈለጉ ፖለቲከኞችን እና ወታደራዊ መኮንኖችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የትግራይ ሕዝብ እንዲተባበር ፖሊስ ጥሪ አድርጓል፡፡

7፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ለጥር 9 የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳራዘመ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ ሰልፉ ከከተራ በዓል ዋዜማ ጋር በመገጣጠሙ እንደተራዘመ ተገልጧል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ጥር 23 አደርጋለሁ ብሏል፡፡ የሰልፉ ዐላማ፣ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለማውገዝ፣ ሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መዳፈሯን ለመቃወም፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ የሚደርጋቸውን ሕገወጥ ግንባታዎች እና የፓርቲው አመራሮች የተፋጠነ ፍትህ አለማግኘታቸውን ለመቃወም ነው፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
9.5K views15:52
باز کردن / نظر دهید
2020-12-30 20:32:02 ለቸኮለ! ረቡዕ ታኅሳስ 21/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1. ብሄራዊ ባንክ በትግራይ ክልል በግጭቱ ሳቢያ ተስተጓጉሎ የነበረውን የአሮጌው ብር ለውጥ እንደገና ዛሬ እንደጀመረ ባንኩን ጠቅሶ መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ የአሮጌው ብር መቀየሪያ ጊዜው ከዛሬ ጀምሮ ቅዳሜ እና ዕሁድን ጨምሮ ለ14 ቀናት ይቆያል፡፡ ከ100 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ላለ የብር መጠን ግን መቀየሪያ ጊዜው ከግጭቱ በፊት ተጠናቋል፤ አሁን ብር መቀየር የሚችሉት ከዚያ ጣሪያ በታች የሆነ ብር ያላቸው ብቻ እንደሆኑ ባንኩ አስታውቋል፡፡

2. ወደ መቀሌ እና አላማጣ መስመር የተጓዘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ ሁኔታ ገምጋሚ ቡድን ከመስክ እንደተመለሰ የተመድ አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ወደ ምዕራባዊ ትግራይ የተሠማራው ቡድን ግን ገና ሥራውን አላጠናቀቀም ተብሏል፡፡ ቀደም ሲል የትግራዩን ግጭት ተከትሎ፣ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የተገመተው የተረጅዎች ቁጥር እንደገና ሊያሻቅብ እንደሚችል ሪፖርቱ አክሎ ገልጧል፡፡

3. ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ ለሸገር ተናግሯል፡፡ የሰልፉ ዐላማ በተለያዩ ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ ማውገዝ፣ ሱዳን በድንበር አካባቢ ለምታደርገው እንቅስቃሴ የመንግሥትን ቸልተኝነት መቃወም፣ የእነ እስክንድር ነጋ የክስ ሂደት መጓተቱን መቃወም እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዲስ አበባ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ግንባታዎች መቃወም ናቸው ብሏል ፓርቲው፡፡

4. በጣሊያን ለአፍሪካዊያን ስደተኞች መብት በመሟገት የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ እንደተገኘች ቢቢሲ አማርኛ በሮም የኢትዮጵያ ኢምባሲን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በስደተኛዋ ግድያ አንድ ጋናዊ ስደተኛ ተጠርጥሮ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ ወንጀሉን መፈጸሙን እንዳመነ ተሰምቷል፡፡ ለጊዜው ግድያው ከገንዘብ ጭቅጭቅ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አጊቱ በስደት በምትኖርባት ጣሊያን በእንስሳት ዕርባታ እና ወተት ተዋጽዖ ሥራዋ ዝና ያላት ነበረች፡፡

5. የሕዳሴ ግድብ ድርድር በመጭው ዕሁድ እንዲቀጥል አፍሪካ ኅብረት ለሦስቱ ሀገራት ጥሪ ማድረጉን የግብጽ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲም ትናንት በሰጡት መግለጫ ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ድርድሩ ላንድ ወር የተቋረጠው፣ ሱዳን የአፍሪካ ኅብረት ባለሙያዎች በድርድሩ ጠንካራ ሚና ይሰጣቸው፤ የድርድሩ አካሄድም ይቀየር የሚል ቅድመ ሁኔታ ካሰቀመጠች በኋላ ነበር፡፡ ዐርብ በሚገባው አዲሱ የፈረንጆች ዐመት ዲሞክራቲክ ኮንጎ የአፍሪካ ኅብረትን የወቅቱ ሊቀመንበርነት ቦታ ከደቡብ አፍሪካ ትረከባለች፡፡

6. የሱማሊያ ምርጫ በመንግሥት እና በተቃዋሚ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች አለመግባባት ሳቢያ እንደገና ሊራዘም እንደሚችል ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡ ባለፈው ኅዳር የታቀደው ባለመካሄዱ፣ እንደገና በአዲሱ የፈረንጆች ዐመት እንዲካሄድ አዲስ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቷል፡፡ 2 የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችን እና አንድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ 14 ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች የምርጫ ኮሚሽኑ ስብጥር ካልተለወጠ፣ ራሳቸውን ከምርጫው እንደሚያገሉ ዝተዋል፤ የራሳቸውን የምርጫ ኮሚሽንም አቋቁመዋል፡፡ የጁባላንድ አስተዳደር ደሞ የፌደራሉ ጦር በቅርቡ ከሠፈረበት ከኬንያ አዋሳኝ አካባቢ ካልወጣ፣ ምርጫ በጁባላንድ አይካሄድም ሲል ዝቷል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
10.9K views17:32
باز کردن / نظر دهید
2020-12-30 15:46:28
ለተማሪዎች፣ ለልጆች፣ ለአዋቂዎች

3d Mobile Phone Amplifier

የሞባይሎን ምስል 10.1 inch አጉልቶ የሚያሳይ ልዩ technology፣

-ከስልኮ ለማንበብ ሆነ Movie ለማየት ተመራጭ የሆነ እና Video ሲያዩ #አይኖ ላይ ሊደረስ የሚችልን ጉዳት የሚቀንስ፣ የሚያዩት ነገር የተለየ ጥራት እና ውበት እንዲኖረው የሚያስችል ምርጥ Technology Magnification: 3-4X

ይህ የሚለየው ለአያያዝ በጣም አመቺ እና በማንኛውም ቦታ መጠቀም መቻላችን ነው።
#ባትሪ የለውም፣ አያስፈልገውም።

አ.አ ያሉበት ድረስ እናደርሳለን
በክልል ከተሞች ያላቹ በፖስታ/Express/በtransport መላክ ጀምረናል።

ዋጋ - 1600ብቻ
@AntenehG1 0901882392

""""""""ታማኝነት መገለጫችን ነው።""""""""""
T.me/em_gebeya
9.1K views12:46
باز کردن / نظر دهید
2020-12-29 18:43:10
በአይነቱ ልዩ የሆነ የልጆች ታብሌት
ወድቆ በቀላሉ የማይሰበር፣ ጠንካራ እና አስተማማኝ ባትሪ፣ የራሱ ፕሮቴክተር ያለው።

Storage - 16GB ፣ Ram - 2GB

ልዩ ልዩ የአእምሮ ቅልጥፍናን የሚያሳድጉ አፕሊኬሽኖችና አዝናኝ ጌሞች
አስተማማኝ ባትሪ
ዘመኑ ያፈራው ጠንካራ 7 inch ስክሪን፤
የፊትና የኋላ ካሜራ፤
አዝናኝ ጌሞችና አስተማሪ መተግበሪያዎች፤
የራሡ መጠቀሚያ እስክርቢቶ ያለው፤
ኢንተርኔት Wifi የሚገናኝ
ከፕሌይ ስቶር ላይ ተጨማሪ አፖችን ዳውንሎድ ማድረግ የሚያስችል

Price: 3400ETB

Telegram @AntenehG1
Phonecall 0901882392

ታማኝነት እና ጥራት መገለጫችን ነው።
T.me/em_gebeya
7.9K viewsedited  15:43
باز کردن / نظر دهید
2020-12-28 21:15:32 ለቸኮለ! ሰኞ ታኅሳስ 19/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1. ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሌሎችም ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ ይወያያል ብለዋል።


2፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሕግ የሚያስከብር እና ጸጥታውን የሚቆጣጠር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ሥራ እንደጀመረ የግብረ ሃይሉን ሃላፊ ሜ/ጀኔራል አሥራት ዲኒሮን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ያቋቋሙት ግብረ ሃይል ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፌደራል ሚንስትሮች የተወከሉ ባላስልጣናትን ያቀፈ ነው፡፡ ግብረ ሃይሉ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ምክክሮችን ካደረገ በኋላ፣ ወንጀለኞችን ማደን እንደሚጀመር ሜ/ጄኔራል አሥራት ተናግረዋል፡፡

3፤ ሁለት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ የተጠየቁትን መስፈርቶች ባለማሟላታቸው መሰረዛቸውን ቦርዱ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡ ሕጋዊነታቸው የተሰረዘባቸው የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የሲዳማ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ናቸው፡፡ ቦርዱ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የሰረዛቸው ፓርቲዎች 28 ደርሰዋል፡፡ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የአፋር ነጻ አውጨ ግንባር ፓርቲ እና የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ደሞ እስካለፈው ሳምንት ያላሟሏቸውን መስፈርቶች አሁን አሟልተዋል፡፡

4. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፖሊስ በአዲስ አበባ የሚሰራ ኩመራ ገመቹ የተባለ የካሜራ ባለሙያውን ባለፈው ሐሙስ እንዳሰረበት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የካሜራ ባለሙያው ፖለቲካዊ ወገንተኝነት የሌለው የፎቶ ዘጋቢ እንደሆነ በመጥቀስ እስሩን ያወገዘው ሮይተርስ፣ ኩመራ ለምን እንደታሰረ እንዳልተገለጸለት ዘግቧል፡፡ ባለሙያው ዐርብ’ለት ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶበታል፡፡ ዐለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ቡድን ሲፒጄም በትዊተር ገጹ ባሠፈረው መልዕክት የኩመራን እስር አውግዟል፡፡

5፤ በሱማሌ ክልል እና አፋር ክልል መካከል ሰሞኑን ግጭት ለተከሰተው ግጭት ሁለቱ ክልሎች በኮምንኬሽን ቢሮዎቻቸው ባወጡት መግለጫ ርስበርስ ተወነጃጅለዋል፡፡ የሱማሌ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ የአፋር ታጣቂዎች በሲቲ ዞን አፍደም ወረዳ ሰላማዊ ሰዎችን ገድለውብኛል ሲል ወንጅሏል፡፡ አፋር ክልል በበኩሉ የሱማሌ ታጣቂዎች በገዋኔ ወረዳ ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ብሏል፡፡ በጥቃቱ ስንት ሰዎች እንደተገደሉ ሁለቱም ክልሎች አልገለጹም፡፡


6፤ በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያቋረጠውን አገልግሎት እንደገና እንደጀመረ የመንግሥት ዜና አውታሮች አዲሱን የከተማዋን ከንቲባ ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡ ባንኮች በከተማዋ አገልግሎታቸውን ያቋረጡት፣ በትግራይ ክልል ልዩ ሃይሎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር፡፡

7፤ በሱዳን ዳርፉር ሰሞኑን በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት 15 ሰዎች እንደሞቱ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በዳርፉር የተሠማራው የተመድ እና አፍሪካ ኅብረት ጥምር ሰላም አስከባሪ ሃይል ተልዕኮ በዚህ ሳምንት እንደሚያበቃ ጸጥታው ምክር ቤት ማወጁን ተከከትሎ ነው፡፡ የዳርፉር ግዛት ነዋሪዎች ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከግዛታቸው እንዳይወጡ ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡ የሱዳን ሽግግር መንግሥት በአካባቢው ጦር አሰማራለሁ ብሏል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
8.3K views18:15
باز کردن / نظر دهید